ተዘራ ካሣ አስመጪና ላኪ ድርጅት
ኩባንያችን አስመጪ ላኪ እና አምራች ድርጅት ነው
የ ኢትዮጵያ የከበሩ ድንጋዮች ከ ተዘራ ካሣ አስመጪና ላኪ ድርጅት

ባለ ብዙ ገፅታ የኢትዮጵያ ኢመራልድ፤ ምንም ዓይነት ስንጥቃት የሌለውና በባዕድ ነገር ያልተሞላ፤


የኢትዮጵያ ኦፓል ፣ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ፣ወገል ጤና አካባቢ የሚገኝ (አማራ ክልል ኢትዮጵያ)
ሀገር ውስጥ የምናስገባቸው ዕቃዎች
ወደ ሀገር ውስጥ የምናስመጣቸው ልዩ ልዩ የኢንዱስትሪ ውጤት የሆኑ መሣሪያዎች ፣ በከፊል የተጠናቀቁና ያለቀላቸው የፍጆታ ዕቃዎችን ነው፡፡ የዚህ ዘርፍ ዓይነተኛ ግብና ዓላማ ለተጠቃሚው ሕዝብ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምርቶች እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡
ወደ ውጭ ሀገራት የምንልካቸው ምርቶች
በአሁኑ ወቅት ድርጅታችን ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው የኢትዮጵያ የከበሩ ድንጋዮች ማለትም ኦፓልና ኢመራድ እንዲሁም በኢንዱስትሪያል ማዕድናት ዘርፍ ደግሞ ክሮማይት ፣ኳርትዝ ፣ኮፐር ፣ኒኬል ማንጋኒዝ ፣ታንታለም እና እብነበረድ ለውጭ ሀገር ገበያ መላክ ነው፡፡ የዚህ ዘርፍ አብይ ግብና ዓላማ ሀገራችን ወደ ውጭ የምትልከውን የከበሩ ማዕድናትና የኢንዱስትሪ ግብዓት መጠን ከፍ እንዲል ማስቻልና በዚያውም የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት ነው፡፡
በአምራች ዘርፍ
በአሁኑ ወቅት በዚህ ዘርፍ ትኩረት የተሰጠው ምግብ ነክ ከሆኑት መካከል ፣ብስኩትና ኩኪ እና አቼቶ ያመርታል፡፡ በተጨማሪም የፀጉር ቅባትና ግሪሲሊን እያመረተ የተጠቃሚውን ፍላጎት ለማሟላት ጥረት ያደርጋል፡፡